Fana: At a Speed of Life!

ኤምባሲው በጅቡቲ የኢትዮጵያን “የአረንጓዴ ዐሻራ” ተነሳሽነት ለማስፋት እየሰራች ያለችውን ፈሂማ ሞሐመድ አመሰገነ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቢቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በሀገሪቱ የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ለሆነችው ፊሂማ መሐመድ ምስጋና አቀረቡ፡፡

አምባሳደሩ ፈሂማ ሞሐመድ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሐሳብ መንጪነት የተጀመረውን “የአረንጓዴ ዐሻራ” መርሐ-ግብር በሀገሯ ዕውን ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነት አወድሰዋል።

ፈሂማ ሞሐመድ ፥ ባለፉት 2 ዓመታትም በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የኢትዮጵያ መንግስት ለጅቡቲ ያበረከተውን በሺህዎች የሚቆጠሩ ችግኞች በዋናነት በማስተባበር እንዲተከሉ ማድረጓም ተመልክቷል፡፡

አምባሳደሩ እንደ ፈሂማ ያሉ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት እና ግብርና ላይ የሚሠሩ ንቁ እና ወጣት ጅቡቲያውያንን ለመደገፍ የኢትዮጵያ መንግሥታት ዝግጁ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በአቅም ግንባታ፣ ነፃ የትምህርት ዕድል፣ ሥልጠና፣ ጉብኝት እና በመሳሰሉት ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት፡፡

በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ መካከል አረንጓዴ ኢኮኖሚ ላይ ያተኮረ ውኅደትን መዘርጋት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል፡፡

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በ3ኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር 50 ሺህ ችግኞችን ለመትከል ማቀዱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.