Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጄክት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ተካሄደ

 

 

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጄክት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ በስካይላይት ሆቴል ተካሂዷል፡፡

 

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ እንዳሉት ÷ ፕሮጄክቱ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት በምትዋሰናቸውና ድርቅ በሚያጠቃቸው አካባቢዎች የከርሰምድር ውሃን በዘላቂነት ለመጠቀምና ተደራሽነትን ለማሳደግ የሚያስችል አካል ነው፡፡

 

ፕሮጄክቱ የሚተገበረው ከዓለም ባንክ በተገኘ 210 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን ÷ በ55 ወረዳዎች በውሃ አቅርቦት፤ በ67 ወረዳዎች በከርሰምድር ውሃ አለኝታ ጥናት ማድረግ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በ4 ወረዳዎች ላይ የመስኖ ልማት ስራዎችን ለመተግበር ያለመ ነው ተብሏል ፡፡

 

የፕሮጄክቱ ምዕራፍ አንድ ኢትዮጵያን፣ ኬንያንና ሶማሊያን እንደሚያጠቃልል መገለፁን ከውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

እንደመጀመሪያ በኢትዮጵያ የተለያዩ ድርቅ በሚያጠቃቸው አካባቢዎች ያሉ ማህበረሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግና የ6 ዓመት የጊዜ ቆይታ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡

 

በመርሐ ግብሩ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አይሻ መሀመድ፣ የዓለም ባንክ የስራ ሃላፊዎች እና የክልሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.