ከ23 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድኑ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር አቻ ተለያየ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ ማጣሪያ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አቻው ጋር ዛሬ ያደረገው ጨዋታ ያለ ምንም ግብ 0 ለ 0 ተጠናቀቀ፡፡
አንደኛ ዙር የመጀመሪያ ማጣሪያ ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የተካሄደ ሲሆን÷ ጨዋታው ያለምንም ግብ ተጠናቋል፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ የመልስ ጨዋታውን መስከረም 27 ቀን 2015 ዓ.ም በኪንሻሳ እንደሚያደርግ መገለጹን ከእግር ኳስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡