Fana: At a Speed of Life!

ተመድ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፉን ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) በኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሚያደርሰውን ሰብዓዊ ድጋፍ ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኑን ገለጸ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽኅፈት ቤት ኃላፊ ማርቲን ግሪፍትስ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይታቸውን ያካሄዱት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከሚካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን መሆኑንም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ የሚያመላክተው፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን ÷ በኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሚደርሰውን ሰብዓዊ ድጋፍ ማሳደግ እንደሚገባ በውይይታቸው አስምረውበታል።

የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽኅፈት ቤት ኃላፊ ማርቲን ግሪፍትስ በበኩላቸው “ኦቻ” ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ይበልጥ በትብብር ለመሥራት እና ድጋፉን ለማሳደግ ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን የሶማሊያ አቻቸውን አግኝተው በሁለትዮሽ የሀገራቱ የጋራ ተጠቃሚነት ላይ እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውም ነው የተመለከተው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.