Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ 8ኛውን የኢትዮ-ሩሲያ የጋራ መድረክ ለማስተናገድ ዝግጅት እያደረገች ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው የ8ኛው የኢትዮ -ሩሲያ የጋራ የምጣኔ ሃብት የምክክር መድረክ ዝግጅት የሚያግዝ ውይይት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተካሄዷል።
የትብብር መድረኩን የሚመሩት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ÷በመድረኩ አስፈላጊነትና ከኢትዮጵያ በሚጠበቁ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር መክረዋል፡፡
ውይይቱ ከዚህ ቀደም በፒተርስበርግ በተካሄደው 7ኛው የኢትዮ-ሩሲያ የጋራ መድረክ የተወሰኑ፣ የተያዙና ቀጣይ ውሳኔ በሚያስፈልጋቸው የምጣኔ ሃብት፣ የሳይንቲፊክ፣ የቴክኒካልና የንግድ ትብብር ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ሚኒስትሩ ለስምንተኛው የጋራ ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት ተሳታፊ የመንግስት አካላት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
በመድረኩ በአዘጋጅ ኮሚቴው ምክክር ከ7ኛው የጋራ መድረክ ወዲህ የተከናወኑ ተግባራት፣ የጋራ ኮሚሽኑ ዓላማና በቀጣይ የሚደረጉ ተግባራትን የተመለከተ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የምክክር ኮሚሽኑ ጉባኤ በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የቆየ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ፥ ኢትዮጵያ በቀጣይ ታህሳስ ወር ጉባኤውን ማስቀጠልና ማስተናገድ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት መጨመር የሚያስችሉ ውጤቶች እንዲገኙ የኮሚቴ አባላት ተገቢውን ትኩረት ሊሰጡ ይገባል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከሩሲያ የማዕድን ሃብት ኤጀንሲ ዋና ሹም ኤቭጅኒ ፔትሮቭ ጋር በበይነ መረብ ትውውቅና ውይይት ማድረጋቸውንም ጠቁመዋል፡፡
በሰባተኛው ኢትዮ-ሩሲያ ኢንተር-ገቨርንመንታል ኮሚሽን ውይይት የተመለከተ መነሻ ነጥብ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መቅረቡም ተመላክቷል፡፡
 
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.