Fana: At a Speed of Life!

ባል ሚስቱን ዘረፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ባል ሚስቱን የዘረፈበት ልዩ ክስተት ተሰምቷል፡፡
መስከረም 11 ቀን 2015 ምሽት 3 ሰዓት አካባቢ በክፍለ ከተማው ወረዳ 11 አስተዳደር የቀጠና 1 ብሎክ 4 የበጎ ፈቃድና የሕዝባዊ ሰራዊት ስምሪት ተሰጥቶአቸው አካባቢያቸውን በመጠበቅ ላይ ነበሩ፡፡
በዚህ ምሽትም አንድ ግለሰብ ከተበዳይ እጅ ሞባይል መንትፎ ሲሮጥ አካባቢውን በመጠበቅ ላይ ያለው ህዝባዊ ሰራዊት በቁጥጥር ስር በማዋል ለፖሊስ ያስረክበዋል።
ሞባይል ዘራፊው ባል ሲሆን÷ ተዘራፊዋ ሚስት መሆኗ ብዙዎችን አጀብ አሰኝቷል።
ይህን አስገራሚ ክስተት እንደምሳሌ ማቅረቡን መረጃው ጠቅሶ÷ ለጸጥታ ሃይሉ አጋዥ ሆኖ አካባቢውን እየጠበቀ ያለው ህዝባዊ ሰራዊት በርካታ ሰርጎ ገቦችንና ወንጀል ፈጻሚዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለ ነው ብሏል፡፡
ህዝባዊ ሰራዊቱ የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ እያበረከተ ላለው አስተዋጽኦ ክብርና ምስጋና ከአካባቢው ማህበረሰብና ከአስተዳደሩ ተሰጥቶታልም ነው የተባለው፡፡
በዚሁ አጋጣሚ ለህዝባዊ ሰራዊቱ ምስጋና ማቅረቡን ከከተማው ብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
‘‘አሁንም አካባቢያችን ነቅተን እንጠብቅ“ የሚል መልዕክት አስተላልፏል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.