ለደመራና መስቀል በዓል የንግዱ ማህበረሰብ የዋጋ ንረትን እና የፀጥታ ስጋቶችን በንቃት መከታተል አለበት- ም/ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ቅርስ የሆነው የደመራ እና መስቀል በዓል ሲከበር የንግዱ ማህበረሰብ የዋጋ ንረትን በመቆጣጠር እና የፀጥታ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ድርጊቶችን በንቃት መከታተል እንዳለበት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ አሳሰቡ፡፡
የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ከአዲስ አበባ የንግዱ ማህበረሰብ ጋር የራሱን ሚና በሚወጣበት ዙሪያ ዛሬ ውይይት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ የዓለም ቅርስ የሆነው የመስቀል በዓል ሲከበር የንግዱ ማህበረሰብ የዋጋ ንረትን በመቆጣጠር እንዲሁም የፀጥታ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ድርጊቶችን በንቃት መከታተል አለበት፡፡
በግንባር ሽንፈት የገጠማቸው የሽብር ኃይሎች ሽንፈታቸውን ለማካካስ፣ የዐደባባይ በዓላትን ሊያውኩ የሚችሉበት መንገድ እንዳይኖር የንግዱ ማህበረሰብ ከፀጥታ አካላት ጋር በትብብር መሥራት እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ገቢዎች ኃላፊ ሙሉጌታ ተፈራ ሰላም ወዳድ የሆነው የከተማዋ የንግዱ ማህበረሰብ የዓለም ሰዎች ሁሉ በዓል የሆነው የመስቀል በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ በበኩላቸው÷ ያለ እምነት ልዩነት የደመራ ቦታን ከማፅዳት ጀምሮ በዓሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የንግዱ ማህበረሰብ በአብሮነት መሥራት አለበት ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!