Fana: At a Speed of Life!

ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች ለራቁ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የትራንስፖርት ወጪ ይሸፈናል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲ ከ50 ኪሎ ሜትር በላይ ለሆነ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የትራንስፖርት ወጪን ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች እንደሚሸፍኑ ተገለጸ፡፡

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በሁለት ዙር ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና በቂ ቅድመ ዝግጅት አድርጌያለሁ ብሏል ።

በዚህም ፈተና ማተምን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች ከወዲሁ መጠናቀቃቸውን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ትራንስፖርትን በተመለከትም ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች በ50 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ ያሉ ተፈታኝ ተማሪዎች ወጪን በራሳቸው እንደሚሸፍኑም ነው የተገለጸው።

ሆኖም ከ50 ኪሎ ሜትር ርቀት በላይ የሚገኙ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች እንደሚያመቻቹ ተጠቁሟል፡፡

ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ የሚፈቀዱላቸውና የሚከለከሏቸው ቁሳቁስም በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡

መጽሐፍትን፣ ሲያጠኗቸው የነበሩ ማስታወሻወች፣ የንጽህና መጠበቂያዎችና የሌሊት ልብስ ከተፈቀዱት ቁሳቁስ መካከል ሲሆኑ ፥ ማንነታቸውን የሚገልጽ የቀበሌ መታወቂያ፣ የመፈተኛ ካርድ ወይም አድሚሽን ካርድ መያዝም ይኖርባቸዋል።

በአንጻሩ ማንኛውንም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ከጋብቻ ቀለበት ውጪ የተለየ ፈርጥ ያላቸው ቀለበቶች፣ ሀብሎች ፣ የጸጉር ጌጦች እንዲሁም ድምጽ የሚያወጡ ጃኬቶች ደግሞ መያዝ አይቻልም ነው የተባለው።

በተጨማሪም የመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የመኝታና የምግብ አገልግሎት እንደሚያመቻቹ ተጠቅሷል።

በመሳፍንት እያዩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.