የሀገር ውስጥ ዜና

የዓለም የቱሪዝም ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በአሶሳ ከተማ እየተከበረ ነው

By Shambel Mihret

September 23, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የቱሪዝም ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ ጊዜ “አዲስ እሳቤ ለቱሪዝም ” በሚል መሪ ቃል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ በሚገኘው በዚህ በዓል ላይ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊን ጨምሮ የተለያዩ የፌደራልና የክልሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ዘርፉ በኮቪድ 19 እና በጦርነት ከደረሰበት ጉዳት እንዲያገግም የሚያስችል ሀገር አቀፍ የቱሪዝም ንቅናቄ እንደሚጀመርም ይጠበቃል።

የዓለም የቱሪዝም ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መከበሩ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ለሚሰራው ስራ እንዲሁም የክልሉን የመስህብ ስፍራዎች ከማስቀዋወቅ አንፃር አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

በላምሮት የኔዓለም