Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል ደመራ በዓልን በተመለከተ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መስቀል ደመራ ለአንድነትና ለሰላም በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አዘጋጅነት የፓናል ውይይት እየተደረገ ነው።

የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም እንዲከበርና ሀይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ለትውልድ ማስተላለፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ነው ውይይት እየተደረገ የሚገኘው፡፡

የፓናል ወይይቱን ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው በዚህ ወቅት እንዳሉት የመስቀል ደመራ በዓል የኢትዮጵያን ምድረ ቀደምትነት ከሚመሰክሩ በዓላት አንዱ ነው፡፡

የዚህ የፓናል ወይይቱ አላማም ቅርስነቱ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ብሎም የዓለም ቅርስ መሆኑ ታውቆ ጥበቃ እንዲደረግለት ግንዛቤ መፍጠር ነው ብለዋል።

በፓናል ውይይቱ የሀይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በታሪኩ ለገሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.