Fana: At a Speed of Life!

20 ሜጋ ዋት የከርሰምድር እንፋሎት ኃይል መገኘቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአሉቶ ላንጋኖ ጥልቅ የከርሰ ምድር እንፋሎት ቁፋሮ ፕሮጀክት እስካሁን 20 ሜጋ ዋት የሚደርስ የእንፋሎት ኃይል መገኘቱ ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአሉቶ ጂኦተርማል ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ መሳይ ፍቃዱ እንደገለፁት÷ እስካሁን ቁፋሯቸው ከተጠናቀቀና የምርት ፍተሻ ከተደረገላቸው አምስት ጥልቅ ጉድጓዶች መካከል በአራቱ 20 ሜጋ ዋት የእንፋሎት ኃይል ተገኝቷል፡፡

የጉድጓዶቹ ጥልቀት ከ2 ሺህ 700 እስከ 3 ሺህ ሜትር እንደሚደርስ ጠቅሰው÷ የ6ኛ እና የ7ኛ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራም እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

ሥራውም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘና የከርሰምድሩን የእንፋሎት መጠን ጥራትና ተደራሽነት ከማረጋግጥ አኳያ እየተካሄደ መሆኑን የኤሌክትሪክ ኃል መረጃ ያመላክታል፡፡

ሥራውም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘና የከርሰምድሩን የእንፋሎት መጠን ጥራትና ተደራሽነት ከማረጋግጥ አኳያ እየተካሄደ መሆኑን የኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ ያመላክታል፡፡

በአሉቶ 1 የከርሰ ምድር እንፋሎት ቁፋሮ ፕሮጀክት እስካሁን ከተገኘው 20 ሜጋ ዋት የእንፋሎት ኃይል በተጨማሪ 15 ሜጋ ዋት እንፋሎት ለማግኘት የሚያስችሉ ከ 2 እስከ 4 የሚሆኑ ጥልቅ ጉድጓዶች መቆፈር እንደሚያስፈልግ ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

የጉድጓዶቹ ቁፋሮ ሥራ እንደተጠናቀቀ ወደ ኃይል ማመንጫ ፋሲሊቲ ግንባታ ፕሮጀክት እንደሚሸጋገርም ጠቁመዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.