የሀገር ውስጥ ዜና

ሴት ሚኒስትሮች የግብርና ማሳዎችን እየጎበኙ ነው

By Mikias Ayele

September 23, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ሴት ሚኒስትሮች በጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ተገኝተው የመኸር የግብርና ማሳዎችን እየጎበኙ ነው፡፡

በጉብኝቱ ላይ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣የከተማና ቤቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ እና የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል እና ሌሎችም የዞኑና የወረዳው ከፍተኛ አመራሮች ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው።

በወረዳው በግብርናው ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች የአርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል መባሉን ከጉራጌ ዞን ኮሙንኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!