የሀገር ውስጥ ዜና

የምዕራብ ኦሞና ካፋ ዞኖች ለሰራዊቱ ከ38 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረጉ

By Melaku Gedif

September 23, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የምዕራብ ኦሞና ካፋ ዞኖች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ38 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረጉ፡፡

የካፋ ዞን ከ31 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን÷ድጋፋን የዞኑ የመንግስት ተጠሪ አቶ አስረስ አስፋው ለመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሊውጂ አስረክበዋል።

በተመሳሳይ የምዕራብ ኦሞ ዞን ደግሞ ከ 6 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ዞኖቹ በቀጣይ ለመከላከያ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!