Fana: At a Speed of Life!

እየለሙ ያሉ የመስህብ ስፍራዎች በዘርፉ ያለውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የመንግስትን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ ናቸው- አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ

 

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ እየለሙ ያሉ የመስህብ ስፍራዎች በዘርፉ ያለውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የመንግስትን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ መሆናቸውን የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ገልፀዋል።

 

የዓለም የቱሪዝም ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በገተኙበት በአሶሳ እየተከበረ ነው፡፡

 

ቀኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲከበር ዘርፉ የሚኖረውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅኦ ለመጨመር የሚያስችሉ ግንዛቤዎችን በህብረተሰቡ ዘንድ ለማስፋት መሆኑን ሚኒስትራ ገልጸዋል።

 

የቱሪዝም ሚኒስቴር ዘርፉን በተለየ እይታ በማጤን ስትራቴጂዎችን በመቀየስ ላይ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

 

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በበኩላቸው÷ በሀገር የኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ የቱሪዝም ዘርፍ ልማትን ከልማዳዊ አሰራሮች ማላቀቅ መቻል የዘርፉ የስኬት ጉዞ መገለጫ መሆኑን ጠቁመዋል።

 

በክልሉ ያሉ የመስህብ ስፍራዎችን ማልማት ከተቻለም ከቱሪዝም ብዙ ማትረፍ ይቻላል ነው ያሉት፡፡

 

የዓለም የቱሪዝም ቀን በአሶሳ መከበሩ የክልሉን መስህቦች ለማስተዋወቅ፣ የታላቁ የህዳሴ ግድብን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰፊ ትኩረት እንዲያገኝ፣ የኢንቨስትመንት እድሉን ለማስፋት እንደሚያግዝም ነው የተናገሩት።

 

ዘርፉ በኮቪድ እና በጦርነት ከደረሰበት ጉዳት እንዲያገግም የሚያስችል ሀገር አቀፍ የቱሪዝም ንቅናቄ እንደሚጀመርም ተመላክቷል፡፡

 

ንቅናቄው የሀገር ውስጥ ጎብኚ ቁጥርን እና ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ በመጨመር ወንድማማችነትን ለማጎልበት ያለመ ነው ተብሏል፡፡

 

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያሉ የጎብኚ መዳረሻዎችን ማስተዋወቅ የሚያስችሉ መርሐ ግብሮች እስከ መስከረም 15 ቀን ድረስ በስፋት ይከናወናሉም ነው የተባለው፡፡

 

በሜሮን ሙሉጌታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.