Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በአውሮፓ ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በአውሮፓ ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዴቪድ ማካሊስተር የተመራውን ልዑክ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

የልዑካን ቡድኑ÷ የአውሮፓ ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ፣ የአውሮፓ ፓርላማ የሴቶች መብትና  የፆታ እኩልነት ኮሚቴ እና የልማት ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢን ያካተተ ነው፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና በአፍሪካ ሕብረት ስለሚመራው የሰላም ንግግር ዙሪያ ምክክር ተደርጓል፡፡

የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት መረጃ እንዳመላከተው÷ የአውሮፓ ሕብረት አምባሳደር ሮናልድ ኮቢያ ከልዑኩ ጋር ተገኝተው በውይይቱ ተሳትፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.