Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅቷን አጠናቃ የዝግጅት ስራው እየተገባደደ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማ እንዲሆን የተለያዩ ተቋማት እና የሲቪክ ማህበራት ድጋፍ ማድረጋቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ድርጅቶች ህብረት ዳይሬክተር አቶ መስዑድ ገበየሁ በምክከሩ የህብረተሰቡ ድምጽ የሚሰማበት፥ ለሰላም እጦት እና ለሰብአዊ መብት ጥሰት መነሻ የሆኑ ችግሮች ተፈተው መፍትሄ እንዲያገኙ እደርጋለን ብለዋል፡፡

የሲቪክ ማህበራቱ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ጋር በጋራ እየሰራን ነው ያሉ ሲሆን በቀጣይም በአመቻች፣ በአወያይ እና በቴክኒክ ድጋፍ ማድረጋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡

ሀገራዊ ምክክሩ የተሳካ እንዲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ አቅሙ በፈቀደው ሁሉ የበኩሉን እንዲያደርግ የሲቪክ ማህበራቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአልማዝ መኮንን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.