Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ የደልሂ ግማሽ ማራቶን አምባሳደር ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በህንድ ዴልሂ በፈረንጆቹ ጥቅምት 16 የሚካሄደው ግማሽ ማራቶን ዓለም አቀፍ ዝግጅት አምባሳደር ሆኗል፡፡

የህንዱ የስፖርት መፅሄት የሆነው ዘ ሂንዱ እንዳስታወቀው የሁለት ጊዜ የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊው ኃይሌ ገብረሥላሴ በፈረንጆቹ ጥቅምት 16 ቀን በሚካሄደው የቬዳንታ ደልሂ ግማሽ ማራቶን አምባሳደር ሆኖ ተመርጧል፡፡

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በተለያዩ ውድድሮች 27 ጊዜ ክብረ ወሰን መስበር የቻለ ሲሆን ይህም በረጅም ርቀት የምንጊዜውም ምርጡ አትሌት ያደርገዋል ብሏል ዘገባው።

እንደ ዘገባው አትሌት ኃይሌ የደልሂ ማራቶን አምባሳደር ሆኖ በመመረጡ ደስተኛ መሆኑን እና ሯጮችን ለማበረታታት ውድድሩ በተያዘለት ቀነ ቀጠሮ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

የደልሂ ግማሽ ማራቶን ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ ውድድር ሲሆን የኡጋንዳው የግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት ጃኮብ ኪፕሊሞን ጨምሮ ሌሎች ስመጥር አትሌቶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.