Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የመስቀል በዓል ተከብሮ እስኪጠናቀቅ የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴ እንዳይኖር ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፊታችን ማክሰኞ መስከረም 17 የሚከበረው የመስቀል በዓል በሰላም ተከብሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴ እንዳይኖር ተወስነ።

የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ እሁድ ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ማክሰኞ መስከረም 17 ማታ 12:00 ድረስ ምንም አይነት የሞተር እንቅስቃሴ በከተማዋ የተከለከለ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በዚህም የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጉ ብሏል ኤጀንሲው፡፡

ይሄንን ተላልፈው በሚገኙ ሞተረኞች ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ጭምር ማሳሰቡን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.