Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል የብሔረሰቦችን የዘመን መለወጫ በዓላት ባህላዊ እሴት ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የሚከበሩ የብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ በዓላትን ባህላዊ እሴት ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡

የህዝብ በዓላት ከዘመን መለወጫነት ባለፈ ለስራ ባህል ግንባታ፣ ለሰላምና አንድነት ምሶሶ ሆነው የማገልገል ተፈጥሯዊ ሚና ያላቸው በመሆኑ ለትውልድ እንዲተላለፉና በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲተዋወቁ እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል።

የቢሮው ሃላፊ አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ ለኢዜአ እንዳሉት በክልሉ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ብሔረሰቦች የየራሳቸው የዘመን መለወጫ በዓላት አላቸው።

የዘመን መለወጫ በዓላትን ከሚያከብሩ የክልሉ ብሔረሰቦች መካከል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ከምባታ ጠምባሮ፣ ሀድያ ብሔረሰቦችን ለአብነት ጠቅሰዋል።

በዓላቱ ለሰላምና አንድነት ግንባታ ምሶሶ መሆናቸውን ገልጸው፥ ያላቸውን ተፈጥሯዊ ዕምቅ አቅም አውጥቶ ለመጠቀም እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።

“በቀጣይ እነዚህ በዓላት የጎብኚዎች መስህብ ሆነው እንዲወጡ ፌስቲቫሎችን በማዘጋጀት በልዩ ሁኔታ እንዲከበሩ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል” ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.