Fana: At a Speed of Life!

የጊፋታ በዓል የሩጫ ውድድር በወላይታ ሶዶ ተካሄደ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጊፋታ በዓል የ3 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በወላይታ ሶዶ ከተማ በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል፡፡

 

ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ የተደረገውን የሶስት ኪሎ ሜትር ሩጫ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ አስጀምረውታል፡፡

 

በዓሉን በማስመልከት ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ፥ የወላይታ ብሔር የጊፋታ በዓል ከረዥም ዘመናት ጀምሮ በራሱ የዘመን ቀመር የጨረቃ እሽክርክሪትን በመከተል 12 ወራትን ቆጥሮ አመት የሚለውጥበት ታላቅ በዓል ነው ብለዋል፡፡

 

በዓሉም ጊፋታ ሲሆን አሮጌውን አመት ተሰናብቶ አዲሱን አመት በአዲስ ተስፋ የሚሻገርበት ደማቅ እለት መሆኑንም ጠቅሰዋል።

 

ይህንን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን በዓል በዘንድሮው አከባበር በተለየ መልኩ ለማድመቅ ” ጊፋታን ባለቤቱ ያከብራል” በሚል መሪ ቃል ይከበራል ተብሏል።

 

በዓሉ የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

 

በመለሰ ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.