Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ከ7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረጉ

 

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አደረጉ።

 

ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ አንድነት ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እየታገለ ለሚገኘው ጀግናው ሰራዊታችን ለአበረከታችሁት አስተዋጽኦ ክብር አለን ብለዋል።

 

የደቡብ ኦሞ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ሎቱሩስ ካረ፥ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ደጀንነታችን ለማሳየት ከ7 ሚሊየን 136 ሺህ በላይ ግምት ያለው የአይነት ድጋፍ አድርገናል ሲሉ ገልጸዋል።

 

ድጋፉ የእርድ እንስሳት እና የደረቅ ሬሽን ድጋፍን ያካተተ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.