የሀገር ውስጥ ዜና

የጋሞ አባቶች የሰላም ተምሳሌትነትን የሚዘክር ሐውልት ተመረቀ

By Amele Demsew

September 24, 2022

 

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋሞ አባቶች እርጥብ ሳር ይዘው ሰላም ያወረዱበትን የሰላም እሴት የሚዘክር ሐውልት ተመርቋል።

 

ሐውልቱ 4 ሜትር ከ70 ሴንቲ ሜትር ርዝመት ሲኖረው ሙሉ በሙሉ በፋይበር ግላስ የተሰራ ነው።

 

አጠቃላይ ሥራውን ለማጠናቀቅ አራት ወራት የፈጀ ሲሆን በምረቃ በዓሉ የፌዴራል፣ የክልል እና የዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የሀገር ሽማግሌዎች መገኘታቸውን ከጋሞ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።