Fana: At a Speed of Life!

የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” እየተከበረ ነው

 

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ የሆነው- “ያሆዴ” በዓል በሆሳዕና ከተማ “ሀድይ ነፈራ” በተባለ የበዓሉ ማክበሪያ ስፍራ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።

 

በዓሉ በቅርብና በሩቅ ያሉ ተሰባስበው በጋራና በአንድነት የሚያከብሩት በመሆኑ ከብሔሩ ተወላጆች በተጨማሪ ከአጎራባች ዞኖችና ክልል የመጡ እንግዶች በታደሙበት በተለያዩ መርሐግብሮችም እየተከበረ ነው።

 

በዓሉ የብሔሩ ባህላዊ ትውፊት መገለጫ በሆነው የአባቶች ምርቃት እንዲሁም ውዝዋዜ እና የቁንጅና ውድድርን ጨምሮ በልዩ ለዩ ኩነቶች እየተከበረ ይገኛል።

 

በመርሐ ግብሩ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ፣ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬን ጨምሮ ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች እና በየደረጃው ያሉ አመራሮች ተገኝተዋል።

 

በተጨማሪም ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የወጣቶችና የሴቶች ተወካዮች መታደማቸውን ኢዜአ በዘገባው አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.