Fana: At a Speed of Life!

ወልቂጤ ከነማ የአማራ ባንክ ጣና ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ፣መስከረም 14፣2015 (ኤፍ ቢሲ) ወልቂጤ ከነማ የ2015 የአማራ ባንክ ጣና ዋንጫ ሻምፒዮን ሆኗል።

ክትፎዎቹ የዩጋንዳውን ክለብ ቡል ኤፍ ሲ 2 ለ 1 በማሸነፍ ነው ሻምፒዮን መሆን የቻሉት።

በባህርዳር ስታዲየም በተደረገው የፍፃሜ ጨዋታ ወልቂጤ ከመመራት ተነስቶ በሳሙኤል አስፈሪ እና ጌታነህ ከበደ ሁለት ጎሎች ማሸነፍ ችሏል።

የአማራ ባንክ ጣና ዋንጫ በአራት የሀገር ውስጥ ክለቦች እና በሁለት ተጋባዥ የውጭ ሀገር ክለቦች መካከል ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ ፍፃሜውን አገኝቷል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.