Fana: At a Speed of Life!

የሴቶችና ሕጻናትን ጥቃት ለመከላከል ስትራቴጂክ ዕቅዶችን በአግባቡ መተግበር ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችና ሕጻናትን ጥቃት ለመከላከል የሚዘጋጁ ስትራቴጂክ ዕቅዶች ተግባራዊነት ላይ ክትትል ሊደረግ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡

የሴቶች ኮከስ÷ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ከፍትሕ ሚንስቴር እና ከዓለም ዓቀፍ የሴቶች ድርጅት ጋር በመተባበር በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት ለመከላከል በተዘጋጀው የአምስት ዓመት ብሔራዊ ስትራቴጂ ዕቅድ ላይ ተወያይቷል፡፡

በውይይ ላይ ለስትራቴጂክ ዕቅዱ ግብዓት የሚሆኑ በርካታ ጥቆማዎችና አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡

ሀገሪቱ የሴቶችና ሕጻናትን ጥቃት ለመከላከል የሚያስችሉ ሕገ መንግሥትን ጨምሮ የተለያዩ ሕጎች፣ ፖሊሲዎች፣ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችና ስትራቴጂክ ዕቅድ ቢኖራትም ችግሮቹ ሊቀረፉ አለመቻላቸው በውይይቱ ተገልጿል፡፡

ለዚህም የሚወጡ ስትራቴጂክ ዕቅዶች ተፈፃሚነት ላይ ጥብቅ ክትትል ሊደረግ እንደሚገባ ተሳታፊዎቹ አሳስበዋል፡፡

በስትራቴጂክ ዕቅዱ ውስጥ የሐይማኖት ተቋማት፣ የሚዲያ፣ በሀገር ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ጠቃሚ ማህበራዊና ባህላዊ ዕሴቶች ሚና መታየት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላትም የችግሩን አሳሳቢነት ተረድተው ችግሩን ለመቅረፍ ሊረባረቡ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

በቀጣይም ምክር ቤቱ በሁሉም ተቋማት ላይ በሚያደርገው የክትትልና የቁጥጥር ስርዓት ተፈጻሚነቱን በጥብቅ እንደሚከታተለውና በቅንጅት እንደሚሠራ መግለፁን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.