Fana: At a Speed of Life!

የኢሬቻ በዓል አከባበርን በተመለከተ በሀረሪ ክልል የፓናል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2015 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል አከባበርን በተመለከተ በሀረሪ ክልል የፓናል ውይይት ተካሄደ።

የሀረሪ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ተወላዳ አብዶሽ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ በክልሉ የኢጪታና ኢሌ ባህላዊ ጨዋታዎችን ጨምሮ ሌሎችም የኦሮሞ ትውፊቶችን ለማበልፀግ ለወጣቶች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አብዱልሀኪም ዑመር በበኩላቸው÷ ሁሉም ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ከኦሮሞ ወንድሞቻቸው ጋር በዓሉን በጋራ በማክበር ሀገራዊ አንድነታቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት ጠብቆ ያቆውና ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በወንድማማችነት የኖረበት አኩሪ ባህል መሆኑን በፓናል ውይይቱ ላይ በቀረበ ጥናታዊ ጽሑፍ ተመላክቷል፡፡

በፓናል ውይይቱ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ አባገዳዎችና የተለያዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡

በኢዮናዳብ አንዱዓለም

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.