Fana: At a Speed of Life!

የሀረሪ ክልል፣ ደቡብ ጎንደር ዞንና ደብረማርቆስ ከተማ ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል፣ ደቡብ ጎንደር ዞን እና የደብረማርቆስ ከተማ ለመከላከያ ሠራዊት የአይነት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ክልሉ ድጋፋን ያደረገው በአፋር ክልል ለሚገኘው የሠራዊቱ አባላት ነው።

ግማሽ ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸውን ቁሳቁሶች የሀረሪ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ተወላዳ አብዶሽ፣ የብልፅግና ፖርቲ  የክልሉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱልሀኪም ዑመርና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ወደ አፋር ግንባር ተልኳልል።

የሀረሪ ክልል በሽብርተኛው የህወሓት  ቡድን ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት በዓይነትና በገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

በተመሳሳይ የደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር ለመከላከያ ሠራዊት በ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጭ÷43 የእርድ እንስሳት እና 187 ነጥብ 6 ኩንታል ደረቅ ምግቦች (ሬሽን) ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የሎጀስቲክስ አስተባባሪ ዓለሙ ተዘራ  እንደገለጹት÷ሕዝባችን በማይነጥፈው ደግነቱ ለመከላከያ ሠራዊት ደጀንነቱን እያሳየ ነው።

እንዲሁም ከደቡብ ጎንደር  ዞን ሁሉም ወረዳዎች ሕዝብ የተሰባሰበ ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው 77 ሰንጋዎችና 1 ሺህ 380 በግና ፍየል  ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በግንባር ድጋፉን የተረከቡት የሠራዊቱ አባል የሕዝቡ  ድጋፍ ለሠራዊቱ ትልቅ አቅምና ሞራል በመሆኑ እየተደረገ ላለው ድጋፍ አመስግነው÷ ለሠራዊቱ  አቅም መጎልበት አሁን ያለው ሕዝባዊ  ደጀንነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

 

በኢዮናዳብ አንዱዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.