Fana: At a Speed of Life!

ታላቁ የህዳሴ ግድብ የቱሪዝም እንቅስቃሴን በከፍተኛ ደረጃ የሚያነቃቃ ፕሮጀክት ነው- አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከኃይል ማመንጫነት ባሻገር የቱሪዝም እንቅስቃሴን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያነቃቃ ፕሮጀክት መሆኑን የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ፡፡

አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የየቱሪዝም ሚኒስትሯ ናሲሴ ጫሊን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች 35ኛውን የዓለም የቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ትናንት ጎብኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ በሚይዘው ውኃ ትልቅ የቱሪዝም መዳረሻ እንደሚሆንም ነው የገለጹት፡፡

የቢጀሚዝ ብሔራዊ ፓርክ የግድቡ ውኃ ከሚተኛበት ስፍራ ጋር እንደሚገናኝ ለአብነት ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ የክልሉን የቱሪዝም መዳረሻዎች ከግድቡ የቱሪዝም ዕድል ጋር በማስተሳሰር ከዘርፉ የላቀ ጠቀሜታ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

የኢፌዴሪ የቱሪዝም ሚኒስትር ናሲሴ ጫሊ፣ ታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫነት ባሻገር ዘርፈ-ብዙ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመው፣ ከእነዚህም አንዱ የቱሪዝም ልማት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለዚህም ከወዲሁ ዝግጅት በመደረግ ላይ ነው ያሉት ሚኒስትሯ ፣ በተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተለያዩ ጥናቶች እየተካሄዱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ዘንድሮ “አዲስ እሳቤ ለቱሪዝም” በሚል መሪ ቃል የተከበረው 35ኛው የቱሪዝም ቀን ለሀገራችን የቱሪዝም ልማት ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ለማነሳሳት ያለመ መሆኑንም መግለፃቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.