Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ የባላስቲክ ሚሳኤል አስወነጨፈች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ በዛሬው ዕለት የአጭር ርቀት ባላስቲክ ሚሳኤል ወደ ባህር ማስወንጨፏ ተሰምቷል፡፡

ፕዮንግያንግ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ከቀናት በኋላ  የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ነው የባላስቲክ ሚሳኤል ያስወነጨፈችው፡፡

ከዚህ ባለፈም ድርጊቱ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ በደቡብ ኮሪያ እና ቀጠናው በቅርቡ የሚያደርጉትን ጉብኝት ለመቃወም ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የተወነጨፈው የአጭር ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤል ጃፓን ባህር ውስጥ ከመውደቁ  በፊት 600 ኪሎ ሜትር  ወይም  373  ማይል መምዘግዘጉ ነው የተገለጸው፡፡

ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን የሰሜን ኮሪያን የባላስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፍ ዓለም አቀፉን ህግ የሚጻረር እና ግልጽ ጠብአጫሪ ድርጊት ሲሉ ኮንነዋል፡፡

ሰሜን ኮሪያ በበኩሏ÷ ድርጊቱ  አሜሪካና ቡብ ኮሪያ  በቀጠናው የሚያደርጉትን ትንኮሳ ለመከላከል ብሎም የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስከበር ያለመ ነው ስትል ውንጀላውን ውድቅ አድርጋለች፡፡

በሌላ በኩል የአሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ በቀጠናው ያለውን  ውጥረት ይብልጥ ያባብሳል በሚል ከሩሲያ እና ቻይና  ትችት የቀረበበት መሆኑን አር ቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.