63 ፍሬ ኮኬይን በባህርዳር ከተማ በቁጥጥር ስር ዋለ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 63 ፍሬ ኮኬይን በባህርዳር ከተማ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ፡፡
ኮኬይኑ የብሔራዊ መረጃና ደኀንነት አገልግሎት የመረጃ ኦፊሰሮች ባደረጉት ሚስጢራዊ ክትትል ነው በቁጥጥር ስር የዋለው፡፡
አደንዛዥ ዕፁ መነሻውን አዲስ አበባ ከተማ ባደረገ ተሽከርካሪ ተጭኖ ሲጓዝ ባህርዳር ከተማ ላይ መያዙን ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ታማኝ ምንጮች አረጋግጠዋል።
ኮኬይኑን ለመያዘ በተደረገ የተቀናጀ ክትትል የአማራ ክልል ፓሊስ መሳተፉንና አንድ አዘዋዋሪ ጭምር በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉ ተጠቁሟል፡፡