Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 10 ሺህ በላይ የመስኖ ውኃ ፓምፖች ለአርሶ አደሮች ተከፋፈሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ የተገዙ 10 ሺህ 467 የመስኖ ውሃ ፓምፖች ለአርሶ አደሮች ተከፋፍለዋል፡፡
 
በስነ ስርዓቱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ የግብርና ሚኒስተር አቶ ኡመር ሁሴን እና ሌሎች የፌዴራል እና የክልል የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም አርሶ አደሮች ተገኝተዋል።
 
የመስኖ ፓምፖቹ እስከ 50 ሺህ ሔክታር በመስኖ የማልማት አቅም እንዳላቸው በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል።
 
ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ÷ በዚህ ዓመት በመስኖ ሥራ አብዮት ለመፍጠር ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት መሥራት ይገባቸዋል ብለዋል።
 
ግብርናን በማዘመን የሰፊውን የኅብረተሰብ ክፍል ሕይወት ለመቀየር የክልሉ መንግሥት በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል።
 
በምንይችል አዘዘው
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.