Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠናን ለማሳደግ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል-አቶ አህመድ ሽዴ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠናን ለማሳደግ፣ አገልግሎቱን ለማስፋፋት እና የታለመለት ግብ እንዲሳካ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ሲሉ  የገንዘብ ሚኒስትር አቶ  አህመድ ሽዴ  ተናገሩ፡፡

በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የተመራ የልዑካን ቡድን  የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠናን ጎብኝቷል፡፡

አቶ አህመድ ሽዴ ÷ የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠናን ለማሳደግ፣ አገልግሎቱን ለማስፋፋት እና የታለመለትን ግብ ለማሳካት መንግስት  ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ነፃ ንግድ ቀጠናውን ለማሳደግ እና ለማሻሻል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ  ጥሪ ማቅረባቸውን  ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በጉብኝቱ  የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ እና  የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋርን ጨምሮ ሌሎች  ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.