መስቀል ፈጣሪ ለሰው ልጆች ያሳየው ፍቅር የሚታሰብበት የፍቅር፣ እርቅ እና ይቅርታ በዓል ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መስቀል በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ ፈጣሪ ለሰው ልጆች ያሳየው ፍቅር የሚታሰብበት የፍቅር፣ እርቅ እና ይቅርታ በዓል መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሩ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አያይዘውም “ህዝቡ ለዘመናት ያካበተውን የአብሮ መኖር እሴቶችን አጠናክሮ ሀገርን ለማፍረስ የተነሳውን ጠላት እያሳፈረ እንዳለ ሁሉ፥ በዓሉን ያገኘውን በመካፈል፣ አብሮ በመሆን እርስ በእርስ ጋሻ መሆናችንን ማሳየት ይጠበቅብናል” ብለዋል።
ህዝቡ ከሁሉም በላይ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር መስዋዕትነት እየከፈሉ ያሉ ጀግኖችን በማሰብ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።