Fana: At a Speed of Life!

በዓሉን ስናከብር አካባቢያችንን ከሰርጎ ገቦች በመጠበቅ መሆን አለበት- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደመራና መስቀል በዓልን ስናከብር አካባቢያችንን ለጥፋት ከተሰለፉ ሰርጎገቦች በመጠበቅ ሊሆን ይገባል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ተናገሩ፡፡

አቶ ማስረሻ በላቸው ለክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም÷ በዓሉን ስናከብር አካባቢያችንን ከሰርጎገብ አጥፊዎች በመጠበቅ እና የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

በዙሪያችን ብዙ የተሳሳቱ መረጃዎች እና ከፋፋይ አስተሳሰቦች ተበራክተዋል ያሉት አቶ ማስረሻ÷ ለዚህ ደግሞ ዛሬ ከምንም ነገር በላይ ለእውነት የምንቆምበት ጊዜ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እያንዳንዱ ጭራሮ ተደምሮ ችቦ ፤ እያንዳንዱ እንጨት ተሰብስቦ ደግሞ ደመራን እንደሚሠራው ሁሉ በእኛ አንድነት ሀገራችን የደመራ ምሳሌ ናት ፤እንደ ደመራው ሁሉ አንድ ሆነን ከፊታችን ያለውን የተስፋ ቀን በጉጉት ልንጠባበቅ ይገባናል ነው ያሉት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.