Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ነቢል ከአውሮፓ ኅብረት የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከአውሮፓ ኅብረት የደቡብ ሱዳን ተወካይ አምባሳደር ቲሞ ኦልኮኔን ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
አምባሳደሮቹ በውይይታቸው የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ ምክክር አድርገዋል።
 
አምባሳደር ነቢል ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ ለአካባቢው መረጋጋት ስታደርግ የቆየችውን አስተዋጽኦ አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም አሸባሪው ህወሓት የተኩስ አቁም ስምምነቱን በማፍረስ ለሶስተኛ ጊዜ ጦርነት መክፈቱን እና አሁን ላይ የሰላም ጥሪ አቀረብኩ በሚል ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ለማደናገር እየሞከረ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
 
ይሁን እንጂ መንግሥት አሁንም ለሰላም ዝግጁ መሆኑን ነው አምባሳደር ነቢል ያረጋገጡት፡፡
 
ከዚህ አንጻር ከሰሞኑን ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የባለሙያዎች ቡድን ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ያወጣው ሪፖርት ተአማኒነት የጎደለው፣ የተዛባና ከሙያዊ ሥነ ምግባር ያፈነገጠ መሆኑን ጠቁመዋል።
 
የኢትዮጵያ መንግሥት መሰል ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ሪፖርቶች እውቅና እንደማይሰጣቸው ጠቁመው፥ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ጉዳዩን በተዘባ መልኩ ከመመልከት ይልቅ ገንቢ ሚና እንዲጫወት ጠይቀዋል።
 
አምባሳደር ቲሞ በበኩላቸው÷ በደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት ይገባቸዋል ማለታቸውን በደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.