Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል በዓልን ስናከብር ለመከላከያ ሰራዊት ደጀንነታችንን አጠናክረን በመቀጠል ሊሆን ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል በዓልን ስናከብር ለሀገርና ለህዝብ ህልውና እየተዋደቀ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ደጀንነታችንን አጠናክረን በመቀጠል ሊሆን ይገባል ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ለደመራና መስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም÷ የመስቀል በዓል ለሀገራችን ህዝቦች ባህላዊ እሴት በመሆን ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ፤ በዓሉ ከሃይማኖታዊ ተልዕኮው ባሻገር ለኢትዮጵያ ህዝብ ባህላዊ ቅርስና ውርስ ነው ሲሉ አውስተዋል።

መስቀል የብሩህ ተስፋ፣ የብርሐንና የድል ምልክት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ደመራ ደግሞ የአንድነት እና የህብረት ተምሳሌት ነው ብለዋል።

በመሆኑም እንደ ሀገር የገጠሙን ችግሮች በጋራ ታግለን ለድል መብቃት የምንችለው በአንድነትና በትብብር መቆም ስንችል መሆኑን መረዳት ይኖርብናል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ።

አያት ቅድመ አያቶቻችን በአንድነት ተሳስረው ጠላትን እየመከቱ ዛሬ የምንኮራበትን ታላቅ አገር እንዳወረሱን ሁሉ ዛሬም ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከአሸባሪው የህወሓት ቡድን ጋር በፍጹም የሀገር ፍቅር ስሜት እየተፋለመ ይገኛል ብለዋል።

በመሆኑም አሸባሪው ህወሓት በእብሪት የከፈተብንን ወረራ ቀልብሰን የሀገራችን እና የህዝባችን ሰላምና ነጻነት ለማረጋገጥ በጽናት የምንታገልበት፣ ለሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ደጀንነታችን በተግባር የምናሳይበት፤ በሌላ በኩል ደግሞ የጀመርናቸውን የልማት ስራዎችን ለስኬት እንዲበቁ በጋራ ርብርብ የምናደርግበት ሊሆን ይገባል ሊሉ አጽንኦት ሰጥተዋ።

ስለሆነም የመስቀልን በዓል ስናከብር ለሀገርና ለህዝብ ህልውና ከጠላት ጋር እየተዋደቀ ለሚገኘው ለሀገር መከላከያ ሰራዊት በሁሉም ዘርፍ ደጀንነታችን አጠናክረን ልንቀ ጥል ይገባል ብለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል የመስቀል በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነትና አንድነት እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.