Fana: At a Speed of Life!

የፓውንድ ዋጋ ማሽቆልቆሉ ተነገረ

የፓውንድ ዋጋ ማሽቆልቆሉ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2015 ( ኤፍ ቢ ሲ)ከዶላር ምጣኔ ጋር ሲነጻጸር የእንግሊዙ ፓውንድ ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉ ተነግሯል፡፡

የእንግሊዝ መንግስት ለ50 ዓመታት ገበያው ላይ አድርጎ የማያውቀውን የግብር ቅናሽ ማድረጉ ለፓውንድ ዋጋ መውረድ በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡

በጉዳዩ ላይ የሚመለከታቸው የእንግሊዙ ቻንስለር ክዋሲ ኳርቴንግ ÷ ባለፈው ዓርብ ቃል ከተገባው የ45 ቢሊየን ፓውንድ የግብር ቅናሽ በተጨማሪ ሌሎች የግብር ማስተካከያዎች እንደሚያደረጉ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የዶላር አቅም ጠንካራ ሆኖ በመቆየቱ ሳቢያ ፓውንድ ጫና ውስጥ ወድቆ ቆይቷልም ነው የተባለው፡፡

የፓውንድ ዋጋ አሽቆልቁሎ የሚቀጥል ከሆነ እንደ ዘይት እና ጋዝ ያሉ በዶላር ከውጪ የሚገቡ ምርቶች ዋጋ ሊያሻቅብ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

ከአሜሪካ የሚገቡ የሌሎች ቁሶች ዋጋም እጅግ እንደሚወደድ ከወዲሁ ተሰግቷል፡፡

አሁን ላይ የእንግሊዝ መንግስት የወሰደው የግብር ቅነሳ እርምጃ እንዲሁም የመንግስት ብድር መጨመር በኑሮ ላይ የዋጋ ግሽበት ሊያባብስ ይችላል የሚል ሥጋት እንዲፈጠር ማድረጉም በዘገባው ተመላክተዋል፡፡

በእንግሊዝ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ በሞርጌጅ የቤት ባለቤት የሆኑ ሰዎች የሚከፍሉት ወርሃዊ የቤት ኪራይ ዋጋም ሊወደድ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.