Fana: At a Speed of Life!

ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን የአንድነታችን ማሳያዎች ናቸው – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን የአንድነታችን ማሳያዎች መሆናቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

አገልግሎቱ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለደመራ እና የመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

የመስቀል በዓል በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በደማቅ ከሚከበሩ በዓላት አንዱ ነዉ፡፡ በዓሉ ከባህላዊና ኃይማኖታዊ ክንዋኔነቱ አልፎም ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ከምትታወቅባቸዉ የማይዳሰሱ ቅርሶች መካከልም አንዱ ነዉ፡፡

የመስቀል በዓል በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) የማዳሰስ ቅርስ ተደርጎ በመመዝገቡ ከሀገር አልፎ የዓለም ቅርስ በመሆን ሀገራችን በዓለም አቀፍ መድረክ የምትታወቅበት ሃብታችን ሆኗልም ነው ያለው መግለጫው፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃም የመስቀል በዓል ብሔር ብሔረሰቦችን ከሚያስተሳስሩ ቱባ እሴቶቻችን መካከል ቀዳሚ ስፍራን እንደሚይዝም አውስቷል።

የመስቀልና የደመራ አከባበር ስነስርዓት በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች የሚከበር ታላቅ ባህላዊና ኃይማኖታዊ ክዋኔ በመሆኑ በዓሉ ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክር እንዲሁም የአንድነትና የመቻቻል በዓል መሆኑንም ነው ያነሳው።

በዓሉ ጭጋጋማው የክረምት ወቅት አልፎ በክረምት ወቅት የተራራቁ ቤተሰቦች የሚገናኙበት ወቅት በመሆኑ የመስቀልን በዓል ከሌላው ጊዜ በተለየ ተናፋቂ እንደሚያደርገውም አንስቷል።

በተጨማሪም በዓሉ እንደየ ብሔሩና አካባቢው ቋንቋ በተለያዩ ሥያሜዎች የሚታወቅ ቢሆንም በየአካባቢው በልዩ መገለጫ የሚከበር በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በብዙ ባህላዊ እሴቶች የተጋመዱ ስለመሆናቸው ትልቅ ማሳያ መሆኑንም ነው የገለጸው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.