Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

 

ርዕሰ መስተዳድሩ መስቀል አምላክ ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅር ያሳየበት፤ ይቅርታን ያደረገበት ታላቅ መለኮታዊ አንድምታ ያለውና ፍቅር፥ ሰላም፥ ይቅርታና መተሳሰብ የሚገለፅበት በመሆኑ በዓሉን ስናከብር በጋራ መሰባሰባችን ብቻ ሳይሆን የአከባበር ባህላችን እና እሴታችን የሚደምቅበት ነው ብለዋል።

 

የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ክዋኔ በዩኔስኮ ከማይዳሰሱ ቅርሶቻችን አንዱ ሆኖ እውቅና ያገኘንበት ሲሆን፦ ልንኮራበትና የማንነታችን ድምቀት ስለሆነ ሁሌም ልንንከባከበው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

 

“በአሁኑም ሰዓት ጠላት በሐገራችን ላይ እያደረሰ ያለው እኩይ ሀገር አፍራሽ ሴራ እየመከነ ያለበትና እኛ ኢትዮጵያውያን በአንድነት መቆማችንንና ለሐገራችን ያለንን ታላቅ ፍቅርና የከፈልነውን መስዋዕትነት የሚያመለክት ነው” ብለዋል።

 

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም “እየታየ ያለው ድል የመጣው የአንድነታችን፣ የፍቅራችን፣ የእርስ በርስ መተሳሰባችንና ለሐገራችን የምንከፍለው መስዋዕትነታችን ውጤት በመሆኑ በዓሉን ስናከብር ጀግና መከላከያ ሰራዊታችንን እያሰብንና እያወደስን ሊሆን እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.