Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከተመድ የስራ ሃላፊዎች ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከተመድ የሰብዓዊ እርዳታ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ካትሪን ሶዚና በኢትዮጵያ የአሜሪካ ተራድኦ የልማት ድርጅት ኃላፊ ሴን ጆንስ የሚመራ የዩኒሴፍ፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራም እንዲሁም የኔዘርላንድስና የእንግሊዝ ኤምባሲ የሥራ ኃላፊዎች ልዑካን ጋር ነው የመከሩት፡፡

ምክክሩም በክልሉ እየተከናወነ ያለው የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎችና በክልሉ የሚኖሩ የአቅመ ደካማ ማህበረሰብ ክፍል ኑሮ በሚሻሻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

የሁለቱ ወገኖች የስራ ኃላፊዎች በአስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳዮች ምላሽ በሚሰጥበትና በክልሉ የሚገኙና ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ህይወትን በዘላቂነት የሚቀይርበት ሁኔታዎች ላይ ከመግባባት መደረሱም ነው የተገለጸው።

ከውይይቱ በኋላም ልዑኩ በአዲሱ የርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የአረንጓዴ አሻራ ማሳረፋቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.