የደመራ በዓል በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት ተከበረ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የደመራ በዓል በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት ተከበረ፡፡
በዓሉ በተለይም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በደማቅ ሃይማኖታዊ ስነ- ስርዓት ተከብሯል፡፡
በበዓሉ አከባበር ሥነ-ስርዓቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ጨምሮ ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ፣ ጳጳሳት፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ምዕምናን፣ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት በዓሉን ለመታደም የመጡ እንግዶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል፡፡