Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ተወላጅ ዳያስፖራዎች የክልሉን የሰላምና የልማት ሥራዎች እንደግፋለን አሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ሚኔሶታ የሚኖሩ የሶማሌ ክልል ተወላጅ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ የክልሉን የሰላምና የልማት ስራዎች እንደሚደግፉ ገለጹ።

በሚኒሶታ የሚኖሩት የክልሉ ዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት በሶማሌ ክልል እንዲሁም በሀገሪቱ በሰላም፣ ልማትና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

በሶማሌ ክልል ባለፉት አራት የለውጥ ዓመታት የተገኘውን የሰላም፣ የነፃነት፣ የህዝብ አንድነትና ሁለንተናዊ ዕድገት በዳያስፖራው ዘንድ ትልቅ መነቃቃትን እንደፈጠረ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ በተፈጠረው ምቹ ሁኔታም በክልሉ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ዕድል ከመፍጠሩ ባሻገር ትክክለኛ መረጃዎችን ማግኘት እንዲችሉ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የክልሉ ህዝብና የፀጥታ አካላት በጋራ በመሆን በቅርቡ አሸባሪው የአልሸባብ ቡድን ላይ የወሰዱት እርምጃ እንዳስደሰታቸው ገልፀው ፥ ለድሉ መገኘት አጠቃላይ የአመራሩ ቁርጠኝነት የሚያስደንቅ መሆኑንም ነው ያነሱት፡፡

በቀጣይም የክልሉን ብሎም የሀገር ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ በተለይም ሽብርተኝነትን ለማጥፋት የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም አስታውቀዋል።

በውይይት መድረኩ በርካታ የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች መገኘታቸውንም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.