Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል ደመራ በዓል በጎንደር ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራ በዓል በጎንደር ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።

በዓሉ መስቀልን መሰረት ባደረጉ ዝማሬዎች፣ የወንጌል ስብከት እንዲሁም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች በመስቀል አደባባይ  እየተከበረ ይገኛል፡፡

በደመራ ሥነ ስርዓቱ የሃይማኖት አባቶች ፣ የጎንደር ከተማ ከንቲባን ጨምሮ ሌሎችም የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ የመስቀል ደመራ በዓል በደብረታቦር ከተማ በአጼ ቴዎድሮስ አደባባይ በልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች እየተከበረ ነው።

በበዓሉ ላይ የደቡብ ጎንደር ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አቡነ ሚካኤል፣ የሐገረ ስብከቱ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች የ44ቱ ሊቃውንት ቤተክርስቲያን እና የሰንበት ትምሕርት ቤት መዘምራን እንዲሁም የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.