Fana: At a Speed of Life!

የ18 ሀገራት ኤምባሲዎች ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 17 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያና አሜሪካን ጨምሮ የ18 ሀገራት ኤምባሲዎች ለክርስትና እምነት ተከታዮች የመስቀል በዓል መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ለኢትዮጵያውያን ወንድሞችና እህቶቻችን በዓሉ የደስታ እንዲሆን ተመኝቷል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የመስቀል በዓል የሰላምና የደስታ እንዲሆን ምኞቱን ገልጿል።

ካናዳ፣ ሕንድ፣ እስራኤል፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን፣ ጀርመን፣ ኔዘርላንድስ፣ ዴንማርክ፣ ስዊዘርላንድ፣ ግብጽ፣ ሞሮኮ፣ አልጄሪያ፣ ኢራን፣ ፓኪስታን እና ሜክሲኮ ሌሎች የበዓል መልካም ምኞታቸውን የገለጹ ሀገራት ናቸው።

የመስቀል በዓል በመላ ኢትዮጵያ በተለያዩ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥነ ስርአቶች በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው።

ትናንት የመስቀል ደመራ በዓል በመላ ሀገሪቱ በደማቅ ሥነ ስርአት መከበሩ የሚታወስ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.