አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተወዳጁ አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡
አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ባደረበት ህመም ምክንያት ሕይወቱ ማለፉን የቅርብ ወዳጆቹ ነግረውኛል ሲል ኢፕድ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያ በተፈተነችበት ወቅት እያመመው ግንባር ድረስ በመሔድና በማሰልጠኛም ምልምሎችን በማነቃቃት የሚጠበቅበትን ሀገራዊ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ይታወሳል፡፡
አርቲስት ማዲንጎ በተለያየ ጊዜ በሠራቸው ሥራዎቹ ዕውቅናና ዝናን አትርፏል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ÷ ለቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ እና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!