Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ በማረፉ የተሰማኝ ኀዘን ከባድ ነው ብለዋል፡፡

አርቲስት ማዲንጎ ለሀገሩ በአጭር ዕድሜው ብዙ የሠራ ከያኒ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

አክለውም ሀገር በተደፈረች ጊዜ ሕመሙን እየቻለ ግንባር ተገኝቶ ሠራዊቱን አጀግኗል፤ ሠልጣኞችንም አበርትቷል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡

ነፍሱ በሰላም ትረፍ ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.