Fana: At a Speed of Life!

“ፊደል ተሳስተሃል” ብሎ ተማሪውን የገደለው መምህር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገረ ሕንድ “ፊደል (ስፔሊንግ) ተሳስተሃል” በሚል ምክንያት መምህር ተማሪውን መግደሉ ተሰማ፡፡

የሕንድ ፖሊስ÷ “ሶሻል (social) የሚለውን ቃል ፊደላት በትክክል አልፃፍክም” በሚል ታዳጊ ተማሪውን በመደብደብ ገድሏል የተባለውን መምህር በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡

የ15 ዓመቱ ታዳጊ ኒኪል ዶህሪ በዚህ ወር መጀመሪያ ፈተና ላይ “social” የሚለውን ቃል ሲጽፍ ፊደላትን በመሳሳቱ÷ ራሱን ስቶ እስከሚወድቅ ድረስ በአስተማሪው ድብደባ እንደተፈጸመበት የሟች አባት ለፖሊስ ተናግረዋል፡፡

ታዳጊው በመምህሩ በደረሰበት ድብደባ በሰሜናዊ ዑታር ፕራዴሽ ግዛት በሚገኝ ሆስፒታል በህክምና ላይ እያለ ሕይወቱ ማለፉ ተዘግቧል፡፡

ይህን ተከትሎም ተከሳሹ ከአካባቢው መሰወሩን ፖሊስ ገልጿል ሲል ኤ ኤፍ ፒ ዘግቧል፡፡

የሕንድ ፖሊስ እንደገለጸው ተጠርጣሪው ለጊዜ ከአካባቢው ቢሰወርም በቅርቡ በቁጥጥር መዋሉ እንደማይቀር ገልጿል፡፡

ክስተቱ በሀገሪቱ ተቃውሞ ብሎም ሁከት እና ብጥብጥ ማስነሳቱ ነው የተጠቆመው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.