Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል በዓል በሰላም መጠናቀቁን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 201 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የመስቀል በዓል በሰላም መጠናቀቁን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቢሮው ኃላፊ ግዛቸው ሙሉነህ እንደገለጹት÷ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ከዋዜማው ጀምሮ የተከበረው የመስቀል በዓል በሰላም ተጠናቋል።

የመስቀል ደመራ በዓል ከመስቀል በዓል ዋዜማ ጀምሮ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቆ መከበሩንም ገልጸዋል፡፡

አሸባሪው ህወሓት የሕዝቡን ሰላም ለማደፍረስና የዘላቂ ሰላምና የልማት ግብ ለማደናቀፍ የሚያደርገውን ጥረት በማምከን÷ ሕዝባችን ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶቹን በሰላም እንዲያከብር እንዲሁም የልማት ተጠቃሚነት ዕድሉን ለማስፋት ከምንጊዜውም በላይ በትኩረት ይሠራል ብለዋል፡፡

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የላቀ ሚና ለተጫወቱና ላስተባበሩ የክልሉ የፀጥታ አካላት እንዲሁም መላው ሕዝብ ላደረገው አስተዋጽኦ የክልሉ መንግሥት አመስግኗል፡፡

በቀጣይም በውጪና በውስጥ ፀረ ሰላም ኃይሎች ላይ ለምናደርገው የሕግ ማስከበር ሥራና ክልላችንን ለማልማት በሚደረገው የተቀናጀ ተግባር ሁሉም የተለመደውን አጋርነትና ደጀንነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ሲል የክልሉ መንግሥት ጥሪ አቅርቧል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.