Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን 1ለ 0 ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ23 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 1ለ 0 ተሸንፏል፡፡
ቡድኑ ባሳለፍነው ሐሙስ በአበበ ቢቂላ ስታድየም ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አቻው ጋር ያደረገውን የቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት መለያየቱ ይታወሳል፡፡
ዛሬ ኪንሻሳ ላይ በተደረገው የመልስ ጨዋታ 1 ለ 0 ተሸንፏል፡፡
በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚደረገው የ2023 የአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ውድድር ቅድመ ማጣሪያ ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ወደ ቀጣዩ ዙር ሳያልፍ ቀርቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

 

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.