Fana: At a Speed of Life!

የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አዲስ ካቢኔ አዋቀሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ 22 አባላት ያሉት አዲስ ካቢኔ አዋቀሩ፡፡

ሥልጣን ከያዙ ሁለት ሳምንታት የሆናቸው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፥ ቁልፍ በሚባሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ነው 22 ተሿሚዎችን የሰየሙት፡፡

ፕሬዚዳንት ሩቶ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፥ በምርጫ ወቅት ረዳታቸው የነበሩት መሪጋቲ ጋቻጉዋ በምክትል ፕሬዚዳንትነት ሪጋቲ የሾሙ ሲሆን ፥ ከዚህ ኃላፊነታቸው በተጨማሪ የመንግሥታት ግንኙነትና የሕገ መንግሥታዊ ኮሚሽኖች ሊቀ መንበር ሆነው ያገለግላሉ ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው የተሾሙት ደግሞ የቀድሞው የአገሪቱ ቃል አቀባይ አልፍሬድ ሙቱዋ ናቸው።

ፕሬዚዳንት ሩቶ የትምህርት ፣ ግብርና፣ ንግድ ፣ ጤና፣ አካባቢ ጥበቃ፣ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች፣ መከላከያ ሚንስትሮችንም ሾመዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የትምህርት ፣ ግብርና፣ ንግድ ፣ ጤና፣ አካባቢ ጥበቃ፣ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች እና መከላከያ ሚንስትሮችንም የሾሙ ሲሆን፥ በቀጣይም ሌሎች የመንግስት ሹመቶች ይፋ እንደሚሆኑ ነው ገለጹት፡፡

ፕሬዚዳንቱ “ለኬንያ ህዝብ ቃል የገባነውን ወደተግባር ለመቀየር አዲሱን ካቢኔ በቅድሚያ መዋቀሩ አስፈላጊ ነው” ማለታቸውንም ዘ ኢስት አፍሪካን እና ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.